Call for Youth Researcher

Call for Youth Researcher (ICRW)

የእግር እብጠት ( ሊምፌዴማ) ምንነትና ደረጃዎች

ተላላፊ የዝሆኔ/ሊምፋቲክ ፊላሪያሲስ ወይም ተላላፊ ያልሆነው ዝሆኔ/ፖዶኮኒዮሲስ በሽታ ተመሳሳይ የሆነ የበሽታ ምልክት ያሳያሉ፤ ይህም የእግር እብጠት (ሊምፌዴማ) ነው፡፡ 

->> የፖዶኮኒዮሲስ እብጠት ከታችኛው የእግር ክፍል በመጀመር ወደ ላይ የሚሰፋ ሲሆን ተላላፊ የሆነው ዝሆኔ በሽታ ደግሞ በተቃራኒው ከላይኛው የእግር ክፍል በመጀመር ወደ ታችኛው የእግር ክፍል እየሰፋ የሚሄድ ነው፡፡

->> የፖዶኮኒዮሲስ በሽታ አብዛኛውን ጊዜ በሁለቱም እግር ላይ የሚከሰት ሲሆን ተላላፊ የሆነው የዝሆኔ በሽታ ግን በአንደኛው እግር ላይ ይከሰታል፡፡

 የእግር እብጠት (ሊምፌዴማ) በሽታ የተለያዩ ደረጃዎች ያሉት ሲሆን በዋነኛነትም በሶስት ደረጃዎች ይከፈላሉ፡፡

1) መጠነኛ፡- መጠነኛ፣ ለስላሳ፣ ጠዋት ጠዋት የሚጠፋ ከቁርጭምጭሚት በታች እብጠት
2) መካከለኛ፡- ዘወትር የሚታይ እብጠት መጠነኛ እጥፋት ያለው
3) ከፍተኛ፡- ዘወትር የሚታይ እብጠት ያለው፤ የቆዳው መልክ የተቀየረ፤እብጠቱ እጥፋት ያለው፤ጉብጉብ ያለ ነገር ያለው፤ሸካራ ነገር ያለው)

የእግር እብጠት (ሊምፌዴማ) ያለባቸው ሰዎች በተደጋጋሚ የሚከሰት ምች አደር ተብሎ የሚጠራ አጣዳፊ የሆነ የህመም ስሜት የሚከሰትባቸው ሲሆን ዋና ዋና ምልክቶቹም ያበጠዉ ክፍል ቆዳ መቅላትና ከፍተኛ ህመም፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ማንቀጥቀጥ እና የማስመለስ ስሜት ናቸው፡፡የዝሆኔ በሽታ በበሽታዉ በተጠቁ ሰዎች ላይ ከሚያሳድረዉ ህመምና የአካል ክፍሎች በማሳበጥ የአካል ቅርጽን ከማበላሸት ባሻገር በህመምተኞቹ ግለሰባዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኑሮ ላይ የሚያስከትለዉ ተጽዕኖና ቀዉስ ከፍተኛ ነዉ፡፡ የእግር እብጠቱ በጨመረ ቁጥር እንቀስቃሴን ስለሚገድብ ምርታማነትን በመቀነስ የእለት ተእለት ገቢ ላይም ተጽእኖ ያሳድራል፡፡

 

=======================================

 

 የእግር እብጠት (ሊምፌዴማ) ልየታ፣ ምርመራና ህክምና

=====================================

የፖዶኮኒያሲስና ተላላፊ የሆነው ዝሆኔ ሊምፌዴማ ምርመራ የበሽታውን ምልክቶችን መሰረት ያደረገ ሲሆን ከሌሎች በሽታዎች ጋር በእግር እብጠት ተመሳሳይነት ያላቸውን በሽታዎች (የስጋ ደዌ፣ ኦንኮሰርከያሲስ እና የመሳሰሉት) በመለየት ምርመራውን ማከናወን የሚቻል ሲሆን ከሌሎቹ በሽታዎች ጋር በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚመሳሰል በምርመራ ወቅት በጥንቃቄ መለየት ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም በምርመራ ወቅት የታማሚው ታሪክ (የሚኖርበት ቦታ፣ ጫማ የመጠቀም ልምድ)፣ የእግር እብጠቱ የጀመረበት የሰውነት ክፍልና አካላዊ ምርመራ ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ እንደ አስፈላጊነቱም ከሌሎች በሽታዎች ለመለየት ሌሎች ምርመራዎች ሊያስፈልጉ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎችን ትክክለኛውን ምርመራ እንዲያገኙ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ መላክ አለባቸው።

 

==============

 የሊምፌዴማ ህክምና

============
በበሽታዉ ለተያዙ የህብረተሰብ ክፍሎች አስፈላጊዉን ክብካቤና ትምህርት መስጠት እንዲሁም ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የሊምፌዴማ ህክምና የሚከተሉትን ያካትታል፡-

ሀ/ የእግርን እና ያበጠ የሰዉነት ክፍልን ንፅህና መጠበቅ

እግርን እንዲሁም እብጠት የተከሰተበትን የሰዉነት ክፍል ንጽህና መጠበቅ በባክቴሪያና ፈንገስ አማካኝነት የሚመጣን ተጨማሪ ኢንፌክሽንን ለመከላከል የሚረዳ በመሆኑ ዘወትር ማታ ማታ ከመኝታ በፊት ዉሃና ሳሙና በመጠቀም በንፁህ ጨርቅ ማጠብ ይገባል። ያበጠዉ የሰዉነት ክፍል ለመድረስ የማይቻልበት ከሆነ የቅርብ ቤተሰብን/ዘመድ/ጓደኛን ድጋፍ መጠየቅና በደንብ ማፅዳት ያስፈልጋል፡፡ የቆዳ ድርቀትን ለመከላከል መደበኛ ፈሳሽ ቅባት ወይም ቫዝሊን መጠቀም ይመከራል፤በአቅራቢያው Whitfield ointment የሚገኝ ከሆነ ደግሞ ተመራጭ ነው።

ለ/ እግርንና ሌላም የታጠበዉን የሰዉነት ክፍል በጥንቃቄ ማድረቅ

እግርን ከታጠቡ በኋላ በጣቶች መካከልና ሌሎችም ከእብጠቱ ጋር ለተያያዙ ክፍሎች ትኩረት በመስጠት በንፁህ ጨርቅ ወይም በአየር በመጠቀም ማድረቅ ይገባል፡፡ በየቀኑ ንጽህ ካልሲ እና ጫማ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በእግራቸው እብጠት ያለባቸው ሰዎች በልካቸው ጫማ በማሰራት መጠቀም አለባቸው።

ሐ/ ቀንም ሆነ ሌሊት በመኝታ ወቅት በተቻለ መጠን እግርን ከፍ ባለ ሁኔታ ማኖር

በስራ ወይም በመኝታ ወቅት እግርን ከፍ አድርጎ ማኖር የሰውነትን ፈሳሽ ዝውውር በማሻሻል እብጠቱን ስለሚቀንስ በተቻለ መጠን እግርን ከፍ አድርጎ ማኖር ይገባል፡፡

መ/ በማንኛዉም ሰዓትና ስፍራ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ

እብጠት ያለበትን እግር አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ያበጠዉን የእግር ክፍል ለማሻሻል ይረዳል፡፡ስለሆነም በማንኛዉም ስፍራና ጊዜ በስዕል 13 በሚታየዉ መሰረት እንቅስቃሴ ማድረግ አለባቸው፡፡

ሠ/ አጣዳፊ ህመም ሲሰማ ሊወሰዱ የሚገባቸዉ እርምጃዎች

ህሙማን አጣዳፊ የሆነ የህመም ስሜት (ያበጠዉ ክፍልና ቆዳ ላይ ከፍተኛ ህመም፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ማንቀጥቀጥ ፣ የማስመለስ ስሜት) ሲሰማቸው ከዚህ በታች የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ አለባቸው፡፡

- እግርን በቀዝቃዛ ዉኃ ዉስጥ ማኖር

- በሐኪም የታዘዘ የህመም ማስታገሻ ኪኒን መዉሰድ

-በሐኪም የታዘዘ ቅባት በታመመዉ አካል ላይ በጥንቃቄ መቀባት

- ብዙ ዉኃ መጠጣት

- ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አለማድረግ

 

================================= 

  በማንኛውም መልኩ ማድረግ የማይገቡ ነገሮች፡-

==============================

-በሙቅ ዉኃ መታጠብ                                                 

-ያበጠዉን ክፍል በማከክና በመቧጠጥ ፈሳሽ ለማዉጣት ጥረት ማድረግ

-በሐኪም ያልታዘዘ ቅባት፣ አመድ ወይም ሌላ ነገር መቀባት የተከለከሉ ናቸው።

 

OSSREA Contact Details

Addis Ababa University
Main Campus at Sidist Kilo

P.o.box: 31971
Addis Ababa
Ethiopia


Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
Website: www.ossrea.net
Tel: +251-1-11239484
Fax: +251-1-11223921

 

 

Visit OSSREA on

OSSREA Development Partners

OSSREA acknowledges and highly values and appreciates the continuous support it receives, through out its decades of existence, from the following development partners:

Disclaimer

The information contained in this website is for general information purposes only. Any reliance you place on such information is therefore strictly at your own risk. In no event will we be liable for any loss or damage.

 

This website is based on a template provided by http://www.joomla51.com/

jav scat porn free